የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Apr 26, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 008/2018

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በዚህም መሰረት፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍየሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜበተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ፣የአገር ውስጥ አምራች ወይምገጣጣሚ ወይም የአምራች ህጋዊ ወኪል ማስረጃ( Ietter of authorization) የገጣጣሚ ህጋዊ ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውለድ ይጠበቅባችኋል::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ስነድ TOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል::
  4. ጨረታው ከሚያዝያ 18 ቀን 2018 እስከ ሚያዝያ 27 ቀን 2018 . አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሚያዝያ 27 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም::
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ አራተኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም ::
  7. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል::
  9. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 400,000(አራት መቶ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

አድራሻ፡የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 898 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን

የነበረበት የኪያሜድ ኮሌጅ ህንጻ አራተኛ ፎቅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *