Addis Zemen (Apr 30, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት ፋይናንስ ህጋዊ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የቢሮ ግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት መሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የስራ ፍቃድ።
2. የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ።
3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቲን ተመዝጋቢ የሆነ።
4. በአጠቃላይ ሥራ /ህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭነት ዘርፍ ደረጃ 5 BC/GC እና ከዚያ በላይ የሆነ።
5. ከዚህ ቀደም በዞንና በከተማ ኮን/ሽን ቢሮዎች የግንባታ ውል ያላቋረጡ መሆናቸውን ማስረጃ ከየቢሯቸው ማቅረብ የሚችሉና ካላቸው ከ70% ፍዝካል አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ።
6. ከሚመለከተው አካል የታክስ ክልራንስ ማቅረብ የሚችሉ እንድሁም ለሥራ ዘመኑ አስፈላጊዉን የንግድ ሥራ ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ ዕድሳት ያደረጉ።
ለ. የውድድር ሂደት የጨረታ ሰነድ አቀራረብ መመሪያ__
ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች ዋቻ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት ፋይናንስ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ኮፒ ይዘው በአካል በመገኘት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር / ከፍለው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/cpo/ማቅረብ አለባቸው።
ተጨራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናሺያልና ቴክንካል ዶክሜንት እያንዳንዱን አንድ ኦርጅናል በተጨማሪ ሁለት ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ ያለባቸው ሲሆን እያንዳንዱን ፋይናሺያልና ቴክንካል ዶክሜንት ጥራዞች ኮፒ ለየብቻ በፖስታ እንድሁም ፋይናሺያልና ቴክንካል ዶክሜንት በተመሳሳይ እያንዳንዱን በየራሱ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ ፖስታ አጠቃለው በማሸግ /ቴክንካል/ፋይንሻል ኮፒ እና ቴክንካል/ለፋይናንሻል በማለት በመጨረሻ በጨረታ ማስከበሪያ ሰነድሲ.ፒ.ኦ/cpo/ ጨምረው በእናት ፖስታ በማጠቃለል አሽገው ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው በእያንዳንዱ የታሸገ ፖስታ ላይ ተጫራቾች መ/ቤት ድርጅት ሙሉ ስምና አድረሻ፣ በአጫራቹ መ/ቤትና አድራሻ፤ጨረታው የቀረበበት የፕሮጀክት ስም እንድሁም የዶክሜንት ምንነትና፤መለያ ምሳሌ፡ ቴክንካል ኮፒ፤ ኢርጅናል ፋይንሻል ሲ.ፒ.ኦ/cpo/…ወዘተ በማለት በጉልህ ጽሁፍ ማስፈር፤የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍና መፈረም ይጠበቁባቸዋል።
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም ስማቸውን፤ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ቀን ሃያ አንድ ቀን/ በተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የምቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ላይ በዋቻ ከተማ ፍ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀንና ቦታ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታው የመክፈቻ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘትየጨረታ መክፈቻውን ሥረዓት አያስተጓጉልም። ከላይ የተጠቀሰው 22ኛው ቀን ብሔራዊ ወይም የህዝባዊ በዓል ላይ ወይም ቅዳመና እሁድ ላይ ሆኖ ከተገኘ የጨረታው መዝግያም ሆነ መክፈቻ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይካሄዳል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ይህን ጨረታ አስመልክቶ ለማናቸውም ተጨማሪ መረጃ ከዋቻ ከተማ ፍ/ቤት ፋይናንስ በመድረስ አልያም በስልክ ቁጥር 047-338 0625 በመደወል አስፈላግውን መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የዋቻ ከተማ የመ//ደ/ፍ/ቤት ፋይናንስ