Addis Zemen (Apr 30, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የሚውሉ መድኃኒት፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የመድኃኒት ግዥ ሎት ምድብ ዐ1/2018
- ሎት 2 የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች (ማሽኖች ግዥ) ሎት ምድብ 02/2018
- ሎት 3 የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች ግዥ ሎት ምድብ 03/2018
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
በስራ መስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው። ቼክ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 በመቅረብ ይህ ማስታወቂየ ከወጣበት ቀን በማግስቱ ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናትን በመጠቀም የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በሰም ለብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ፋይናንሻልና ቴክኒካል) በመያዝ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ በአላሙራ የመጀመያ ደረጃ ሆስፒታል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 064 212 9560 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል