Addis Zemen (Apr 30, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሾች እነ ብርሃኔ ሙላባቸው /8 ሰዎች እና በአፈጻጸም ተከሳሾች እነ አቶ ውብሸት ሙላባቸው /6 ሰዎች መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአቶ ሙላባቸው ሃይሌ እና እማሆይ ዘውድነሽ ወ/ማርያም ሃብት የሆነ በደ/ብርሃን ሬጅዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር እምዬ ምኒሊክ ክ/ከተማ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ አታክልት ከተባለ ቦታ ልዩ ስሙ ቃጭሌ ከተባለ ስፍራ በአዋሳኝ ከምስራቅ ፍቅረ፣ ከምእራብ መንገድ፣ ከሰሜን ፍቅረ፣ ከደቡብ አመለወርቅ ማሞ አዋሳኝ መካከል የሚገኝ መጠኑ 0.4 ሄክታር ክልል ውስጥ የሰፈረ ከድንጋይ ግንብ የተሰራ 80 ቅጠል ቆርቆሮ የፈጀ ሁለት ቆርቆሮ ቤት፤ ሁለት የሳር ቤቶችን ቦታውን ጨምሮ በመነሻ ዋጋ ብር 3,000,000/ሶስት ሚሊዮን ብር/ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።
በመሆኑም፡–
- የጨረታው ቀን ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይካሄዳል
- የጨረታው አሸናፊ በሲፒኦ ያሸነፈበትን ዋጋ 1/4 በፍ/ቤቱ ስም ወዲያውኑ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ደ/ብርሃን