Addis Zemen (Apr 30, 2026)
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቀጥር 006/2018
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና ሶፍትዌሮችን መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው።
2. አግባብነት ያለውና ከጨረታው አይነት ጋር የሚጣጣም በዘመኑ የታደሰ የንግድፈቃድ ያላቸው።
3. በታክስ ባለሥልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው።
4. የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
5. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥና ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችላቸው ሕጋዊ ማስረጃ አግባብነት ካለው የመንግሥት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ።
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ላይ ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ያላቸው።
7. መ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር / ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
9. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ከመሥሪያ ቤቱ ግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
10. ተጫራቾች ለመጫረት ዋጋ ያቀረቡባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት
11. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዕለቱ የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የዋጋ /Financial proposal/ እና የቴክኒኩን /Technical proposal | ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻም አራቱንም አንድ ላይ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ሕጋዊ ማህተም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
13. ዘግይቶ የሚመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
14. ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
15. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሳርቤት በሚገኘው የመ/ቤቱ ግምጃ ቤት ገቢ ካደረጉ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
16. ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ሳርቤት፣ ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ የኦሮሚያ ቢሮዎች ያሉበት ግቢ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ነው።
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን