በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 01, 2026)

በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤት ሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣

  •  የታደሰ የዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  •  የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  •  የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል!
  •  የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው!
  •  የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ፤ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡
  • ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒአ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት!
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት!
  • ጨረታው የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡ዐዐ ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  •  የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፐላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ አስ ዋና ሥራ ሂደት ነው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን የደንብ ልብስ ጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108  ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት

ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *