የቤቱ ስፋት 64.4 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤቱ ስፋት 64.4 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (May 01, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፍ/ባለመብት አቶ ጌታሰው አስማረ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ሰለሞን መብራቱ መካከል ስላለው ፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/314949 በ23/4/2016 .ም እና መ/ቁ/316185 በ29/8/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ተማ አስተዳደር በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኝ የጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻ ቁጥር በ308 ቤት ቁጥር 15 የካርታ ቁጥር ኤ/ኪው/2026/23/70461/00 በአቶ ሰለሞን መብራቱ ዘገየ ም የተመዘገበ የቤቱ ስፋት 64.4 ካ/ሜ / አዋሰኞቹ በሰሜን ኮሪደር በደቡብ ቁጥር ቢ308/16 በምስራቅ ኮሪደር በደቡብ ባዶ መሬት የሐራጅ መነሻ 1,938,600 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.PO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤ/ጽ/ስም C.PO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *