በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ የጋርዱላ ዞን የባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ የጋርዱላ ዞን የባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት፡-

የጋርዱላ ዞን የባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN No ያላቸው
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 1,000,000 /አንድ ሚሊየን ብር/ ሲ.ፒ.ኦ / የአልግሎት ጊዜው ከ120 ቀናት በላይ የሆነ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የምችሉ፤
  6. ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ መወዳደር ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር / መግዛት አለባቸው የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በተለያዩ ፖስታ በማሸግና ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ቴክኒካል ላይ ቴክኒካል ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በእናት ፖስታ በማሽግ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ22 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጁ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው 22ኛው ቀን የዕረፍት/የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይታሸጋል
  8. ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስና ፕ/ል/መምሪያ ግዥ ክፍል ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተክንካሉ ይከፈታል
  9. የተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት እያስተጓጉልም።
  10. የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው በተገለፀው 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኃላ በ5 ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
  11. አሸናፊዎች በገቡት ውል መሠረት ግንባታውን በተጠቀሰው ቦታ የመገንባት ግዴታ አለባቸው።

መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰብያ፡-ለማጭበርበር ሙከራ ያደረጉ ተጫረቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ

ለበለጠ መረጃ ስልክ 046 774 0344/343 ደውሎ መጠየቅ ይችላለ

የጋርዱላ ዞን ፋ/ፕ//መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *