Addis Zemen (May 04, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 008
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በዩኒሴፍ ፕሮግራም አዲስ ለሚቋቋሙ 6 የልዩ ፍላጎት /አካቶ ትምህርት/ መስጫ ማዕከላት ለማደራጀት የሚረዱ የአካል መርጃ መሳሪያዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይንም መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
መስፈርት፡–
1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረተት፣አስተማማኝ ዋስትና መስጠት የሚችል፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንዳንድ ኦርጂናል እና ኮፒለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና አብሮ ማቅረብ አለባቸው።
7. መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር– 046-771-0688 መደወል ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ
ወራቤ