Addis Zemen (May 06, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ክብሮም ታረቀኝ ህንጻ ሥራ ተቋራጭ እና የፍርድ ባለዕዳ ሬድ ሲ ጨው ማቀነባበርያ እና ማምረቻ ኃላ/የተ/የግል ማህበር መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር የፍርድ ባለዕዳ እንደፍርዱ ሊፈጽም ስላልቻለ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አፍዴራ ወረዳ የሚገኝ የፍርድ ባለዕዳ ሬድ ሲ ጨው ማቀነባበርያ እና ማምረቻ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ንብረት የሆነ በ36.000ሜ.ካ ያለ ጅምር የጨው ማቀነባበርያ ፋብሪካ ባለበት ሁኔታ መነሻ ግምቱ ብር 19,581,402.38 (አስራ ዘጠኝ ሚልዮን አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አራት መቶ ሁለት ከ38/100) የሆነ ንብረት በግልጽ ጨረታ በሐራጅ ይሸጣል።
- ለንብረቱ መሸጥ ምክንያት የሆነውና በፍርድ የተወሰነው የገንዘብ ልክ ብር 8,146,668.558 (ስምንት ሚልዮን አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስምንት ከ558/100) ነው።
- ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በሚጫረቱበት ወቅት የንብረቱ ግምት 1/4ተኛ በቼክ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በ5 ቀን ውስጥ አጠቃለው ገቢ ማድረግ አለበት አለባቸው።
- የሀራጁ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ አካል በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል ወይም ግዴታውን ሣይፈጽም ቀርቶ ንብረቱ በ2ኛ ጨረታ ቢሸጥ ዋጋው የቀነሰ እንደሆነ ልዩነቱንና ኪሣራውን እንዲከፍል ይገደዳል።
የአውሲ ርሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት