የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ከታች ቀጥሎ በሎት አንድ እና በሎት ሁለት የተዘረዘሩትን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ.ብግጨ/12/2018

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የጨረታ አይነት

 

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ) ብር

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የመዝጊያ ቀን

የመዝጊያ ሰዓት

የመክፈቻ ሰዓት

1

ሎት አንድ

የጥገና ዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች ግዥ

200

100ሺህ

ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

4:00

4:30

2

ሎት ሁለት

የተለያዩ መኪናዎች የመለዋወጫ እቃዎች ግዥ

200

100ሺህ

ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

8:00

8:30

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በዝርዝር እንድተገለፀው እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴከኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፍ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ ቲን ቫት፤ በGP/PA የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባችሁ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ. አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ. ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ከፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በእያንዳንዱ ሎት በተገለፀው ብር መሰረት በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በግልጽ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና (ለ60 ቀናት የሚቆይ) ማስከበሪያ ከላይ በተገለፀው መሰረት በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና ይሆናል ።
  4. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት እያንዳንዱ ሎት-1 እና በሎት-2 ለየብቻ በማድረግ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ።
  5. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሁኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴከኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ፡የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ ቁጥር፡-+251 911 984 467 / +251 913 217 657

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *