በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የደሴ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ የህትመት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የደሴ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ የህትመት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (May 04, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የደሴ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል 2018 በጀት አመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2.የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 4. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 5.የህትመት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡

3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች ውድድሩ በሎት ስለሆነ ከፋፍሎ መሙላት አይቻሉም ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸዉ፡፡

6. ስለ ጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ከፍሎ በመዉሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ስራ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ተእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በማዕከሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገፁ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 1130 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑ በዚህ እለት 1130 ይታሸጋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 330 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ማዕከሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡

11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር +251 333 199 42 ወይም 09 14 87 47 47 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡ ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጎን

የደሴ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *