Addis Zemen (May 07, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን ROTRY DRLLING RIG MACHINERY በዘርፉ ፈቃድ ካሳ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የማሽኑ አይነት |
የማምረት አቅም |
መለኪያ |
ብዛት |
የማቅረቢያ ቦታ |
ምርመራ |
|
1 |
ROTRY DRLLING RIG MACHINERY |
>40M |
በቁጥር |
01 |
ኮርፖሬሽናችን የሚፈልገው ፕሮጀክት ላይ |
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታ መወዳደር ይችላል::
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT) ያላቸው መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲ.ፒ.ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ የተ.እ. ታክስን ጨምሮ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በኮርፖሬሽናችን ስም ማለትም “ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (Hibir Construction Corporation) ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለሚታሰብ ለ90 (ዘጠና) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ “ማስያዝ አለባቸው:
3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለጸው ROTRY DRLLING RIG MACHINERY ቴክኒካል ኦርጅናል (ዋና) እና ኮፒ (ቅጂ) በማለት ለየብቻ እና የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን የፋይናንሻል ፖስታ ኮፒ (ቅጅ) እና ኦርጅናል (ዋና) በማለት በተለያየ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በፖስታ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ።
6. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የእቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል::
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ እና የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በሃያኛ ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ይከፈታል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (058-320-35-76 መደወል ይችላሉ።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር