Addis Zemen (May 07, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MKREU-003/2018
የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስር የሚገኙ ትልልቅ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ቀላል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (አውቶሞቢል እና ዳብል ካፕ ፒከአፕ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት መከራየት ይፈልጋል።
ዝርዝሩም እንደሚከተለው ይሆናል።
|
የጨረታው ቁጥር |
ሎት |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ብዛት |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
|
MKREU-003/2018 |
ሎት 1 |
በኤሌክትሪክ የሚሰራ ዳብል ካፕ ፒክአፕ |
>8 |
ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 8:30 ሰዓት |
ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 9:00 ሰዓት |
|
ሎት 2 |
በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶሞቢል |
4 (እንደ አስፈላጊነቱ ይጨምራል ይቀንሳል) |
ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 8:30 ሰዓት |
ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 9:00 ሰዓት |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፡ ማስረጃ ያለው መሆን አለበት፤
2. በጨረታው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣ መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው እና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4. አድራሻ፡– መቐለ ከተማ ከፕላኔት ሆቴል ብሎ ዛምራ ኮንስትራክሽን ህንፃ ላይ የሚገኘው የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304፣
5. ተጫራቾች ለ120 ቀናት እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት “ለመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት” (MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY) ተከፋይ የሆነ የገንዘብ መጠኑ ሎት1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እንዲሁም ሎት2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ መሆን ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥሩ MKREU-003/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
9. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 342 406 712 መደወል ይችላሉ ።
የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት