የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለታላቁ አንዋር መስጅድ አገልግሎት የሚውል ጄነሬተር እና ሰመር ፓምፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለታላቁ አንዋር መስጅድ አገልግሎት የሚውል ጄነሬተር እና ሰመር ፓምፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AAM 12/2018

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለታላቁ አንዋር መስጅድ አገልግሎት የሚውል ጄነሬተር እና ሰመር ፓምፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

  • ሎት 1 የጄኔሬተር ግዥ ጨረታ ማስከበርያ ብር ——50,000
  • ሎት 2 የሰመር ፓምፕ ግዥ ጨረታ ማስከበርያ ብር—50,000

በዚሁ መሰረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች:

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት መያያዝ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000050280873 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱ በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 413 ለተከታታይ 8 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት (አርብ ዝግ ሆኖ ቅዳሜ ክፍት ነው) መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የቴክኒካልና ዶክመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ እና ፋይናሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ስሙ ጦር ሀይሎች በሚገኘው ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን 430 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ምክር ቤቱ በሚያመቻቸው አዳራሽ 500 ይከፈታል።

5. የጀነሬተሩ እና የሰመር ፓምፑ ዝርዝር መግለጫ በፅሁፍ እና በፎቶ የተደገፈ ካታሎግ ቴክኒካል ዶክመንት ጋር አብሮ መቅረብ አለበት።

6. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም 60 ቀን የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።

7. በጨረታው ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ዋጋ የሚሞላው በም/ቤቱ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።

8. 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ (አርብን ጨምሮ ) በቀጣዩ የመንግስት የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይከፈታል።

9. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት::

11. ምክር ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ::

12. ጨረታው 60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0922 731 627 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *