መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/ ፕሪንተር፣ ኮፒ ማሽን፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ፋክስ ማሽን፣ መታውቂያ ፕሪንተር፣ ፔይሮል ፕሪንተር እና የቢሮ እቃዎች ጥገና አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/ ፕሪንተር፣ ኮፒ ማሽን፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ፋክስ ማሽን፣ መታውቂያ ፕሪንተር፣ ፔይሮል ፕሪንተር እና የቢሮ እቃዎች ጥገና አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 08, 2026)

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ መኢኢግ/ግጨጥ/03/2018

1. የግዥ ፈፃሚው ስም፦ መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/

2. የግዥው ዓይነት:

ሎት አንድ፡ፕሪንተር፣ ኮፒ ማሽን፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፋክስ ማሽን፣ መታውቂያ ፕሪንተር፣ ፔይሮል ፕሪንተር እና የቢሮ እቃዎች ጥገና የአገልግሎት ግዥ

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Number) እና በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት ኦን ላይን የተመዘገበ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደሰትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ኃይሌ ጋርመንት የቀድም ሪቬራ ሆቴል ማግኘት ይችላሉ።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ሎት የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ግዥ የጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታዋች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው ይለቀቅለታል። የአሸናፊ መግለጫ ከተላከና ውል ከፈረመ በኋላ ቢድ ቦንዱን ተጫራቾች መልሰው መውሰድ ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል።

8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበው ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል የድርጅታችሁ ማህተም የተመታበት፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው። እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት አገልግሎት ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልጽ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ቀናት ከጠዋት 230 እስከ 1030 የሥራ መውጫ ባሉት ሰአቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው ቀን 13 ግንቦት 2018 ከጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን 13 ግንቦት 2018 ከጠዋቱ 415 ይከፈታል።

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ()ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም።

12. ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ፡

ስልክ ቁጥር፡– 09 67 26 16 36/

ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴል አዲስ አበባ ፣ኢትዮጵያ

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *