Addis Zemen (May 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጀ ቤት በ2018/ዓ.ም በማዘጋጃ ቤታዊ በጀት የሚከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
I. የጠጠር መንገድ ግንባታ ሥራ፣
1. ከአዲሱ መነኻሪያ እስከ ብርቱ ተስፋ መዋዕለህፃናት የጠጠር መንገድ ግንባታ ጥገና ግንባታ ፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW-01/2025/26፣
2. ከተ/ሀይማኖት አስፋልት መጨረሻ እስከ ሊች አምባ ጤና ጣቢያ እስከ ሶዶ አስፋልት ድረስ የጠጠር መንገድ ግንባታ ጥገና ፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW- 02/2025/26
3. የአፈር መንገድ ጥገና ግንባታ በአራዳ ቀበሌ ፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW-03/2025/26፣
4. ከወልቂጤ አስፋልት እስከ ሀቅ ሙራ መቃብር ድረስ ከድሬኔይጅና ከልቨርት ጭምር የጠጠር መንገድ ግንባታ ፓኬጅ ቁጥር Hossana/MUN/CW-01/2025/26፣
የጨረታ መመሪያ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ ግብር ከፋይነት ማስረጃ፣ የታደሰ ኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ ፣በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት የአቅራቢነት ማስረጃና የተጨማሪ እሴት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ከተራ ቁጥር ከ1 እስከ 3 ድረስ ለተጠቀሱ ደረጃ G.C-6/RC-6 እና ከዚያ በላይ ያላቸው በተራ ቁጥር 4 ያለውን ደረጃ G.C-4/RC-4 እና ከዚያ በላይ ያላቸዉ የጨረታ ሰነዱን ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 32 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 500/አምስት መቶ/ብር በሆሳዕና ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ባለፍቃዱ ወይም ህጋዊ ወኪል ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ የሠነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ21ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ 21ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የዉክልናውን ኦርጅናል ይዞ ሲቀርቡ የሚከፈት ይሆናል፣
- ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች ለተጠቀሱ ፕሮጀክቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፡- 1ኛ. በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ 2ኛ. በማይሻር ሌተር ኦፍ ከሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና ፣ 3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼከ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ፡- ለፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW-01/2025/26 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ)፣ ለፓኬጅ ቁጥር Hossana/MUN/CW-01/2025/26 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ ብር ብቻ)፣ ለፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW-02/2025/26 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር/ብቻ፣ ለፓኬጅ ቁጥር Hossana/GOV/maintenance CW-03/2025/26 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር/ብቻ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
- ማንኛውም ተጫራች ሥራውን የሚሰራበትን የግንባታ ቴክኒካል ክፍል አንድ ኦርጅናል፣ ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ መደበኛ የጨረታ ሰነድ (SBD) እና የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ እንዲሁም የፋይናንሻል ክፍል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዱን በሰም በማሸግ በመጨረሻም ሁሉንም የጨረታ ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ፣ የአጫራች መ/ቤት ስም፣ የፕሮጀክት ስም፣ የፓኬጅ ቁጥር፣ የፕሮጀክት ሳይት እና የተቋራጩ ስም በፖስታዉ ላይ በመጻፍ በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 32 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ሁሉም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም መሳረፍና መፈረም አለበት። ይህ ከልሆነ ከጨረታ ሂደት ዉጪ ያደርጋል።
- ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት ውጪ ከተደረገ በኋላ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
- በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ 10 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፤
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ተጫራች አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለተጨማሪ መረጃ 046 555 1841/ 0472
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት