Addis Zemen (May 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥነ–ምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት በቅጥር ግቢው ውስጥ ሊያሠራ ላቀደው የኮሚሽነር ቢሮና የአዳራሽ ዕድሳት ሥራ ለማሠራት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡–
1. ደረጃቸው GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2018 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው::
3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
4 የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
6. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታከስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 (ሀያ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥነ– ምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን ግዥ/ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ(ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥነ–ምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን ግዥ/ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
10. አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥነ–ምግባር እና የፀረ–ሙስና ኮሚሽን
ሀዋሳ