የቂ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች የመዝናኛ ክበብ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለአባሎች እና ለአመራሮች አገልግሎት እንዲሰጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የቂ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች የመዝናኛ ክበብ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለአባሎች እና ለአመራሮች አገልግሎት እንዲሰጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 08, 2026)

 የጨረታ ማስታወቂያ

የቂ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች የመዝናኛ ክበብ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለአባሎች እና ለአመራሮች አገልግሎት እንዲሰጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0022/2018

በመ/ቤታችን ቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ሎት 1 የቂ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ መዝናኛ ክበብ፤ ባምቢስ ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ክበብ፤ ቄራ ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ክበብ፤ የፖፑላሬ ፖሊስ ጣቢያ የመዝናኛ ክበብ፤ደንበል ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ክበብ፤ ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ክበብ፤ ጎተራ ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ከብብ እንዲሁም የመስቀል ፍላወር ፖሊስ ጣቢያ መዝናኛ ክበብ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለአባሎች እና ለአመራሮች አገልግሎት እንዲሰጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች

  1.  ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፤
  2. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤
  3. የዘመኑን የንግድ ፍቃድ የገበሩ ስለመሆናቸው ወይም ስለመታደሱ እና ተጨማሪ የእሴት ታክስ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ግብር ከፋይ ሙሉን 4X1/አራት በአንድ / ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. በሚጠየቀው መሠረት ለጨረታ የተወዳደሩበትን ጥራት ያለው ያሸነፈበትን አገልግሎት በተሰጠው የጊዜ ገደብና ተወዳድሮ ባሸነፈበት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የክበብ ምግብ እና ትኩስ ነገር አቅርቦት ላይ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቃ አቅራቢዎች ወይም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አይገደዱም
  6. ጨረታውን መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቅዳሜ እና እሁድ ሳያካትት 10 የስራ ቀናቶች ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር በሎት 400 /አራት መቶ ብር/ በየጣቢያዉ በመክፈል ሰነዱ መግዛትና ለጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፤ በዛኑ እለት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አገልግሎት ሎት 1. 1000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ጥቃቅንና አነሰተኛ ከሆኑ ከተደራጁበት ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው ተለይቶ እንደታወቀ በጨረታው ለተሳተፉት ያስያዙትን ጥሬ ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
  9.  መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች  ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት ለመወዳደር የምትፈልጉ እና በሚቀርበው ውል መሠረት ለማቅረብ በደንቡ መሠረት መጫረት የምትችሎ መሆኑን በግልጽ በማመልከት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

አደራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፊት

ለፊት ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ላይ የቀድሞው እስፖርት ፌዴረሽን ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 509

 ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር-01-15-54-68-55/01-1-550-87-39 ደውሎ  ማነጋገር ወይም በአካል ቀርቦ መነጋገር ይቻላል፡፡

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *