Addis Zemen (May 09, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ ቅርንጫፎች በባህር ዳር እና በደሴ የሚገኙ ሲሆን የኦክስጅን ማምረቻ ማሸን ማለትም AirSep oxygen generator, HlX booster and kaeser Air compressor መለዋወጫዎችን መሳሪያዎች ግዥ ስለ ሚያስፈልጋቸው በዘርፉ የተሰማራችሁ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያላቸው
3.ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነትተመዝጋቢከሆኑ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጫረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ውድድሩ በሙሉ ሰርቪስ ማድረግ ስለሆነ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
6. ስለ ጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ |ስፔክ/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በመውሰድየህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
8.ተጫራቾች የጫረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ስራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 3% (ሶስት ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)ዌም በማዕከሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገጹ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተማ ፊርማ እና አድራሻው በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡3ዐ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት 11፡30 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡በዓል ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ማእከሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0583200415/ 0583201992 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0593203088 መጠየቅና ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፣ ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ጎን
ባህርዳር በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል