Reporter (May 10, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።
|
ተራ .ቁ |
የተበዳሪ ስም |
አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አቶ ፀሐይ አንዱአለም ጥሩነህ |
አቶ ፀሐይ አንዱአለም ጥሩነህ |
አቡነ ጴጥሮስ |
አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08፣የቦታ ስፋት 313 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት |
AA000070802136/2157 |
21,301,112.00
|
ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት |
|
አቶ ፀሐይ አንዱአለም ጥሩነህ |
አቡነ ጴጥሮስ |
አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08፣የቦታ ስፋት 171 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ G+3 ቤት |
AA000070805457 |
17,201,656.00
|
ሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
||
|
2 |
ስማያዝ ትራንስአክት ኢንተርናሽል ኃ/የተ/የግ/ማ/ |
ስማያዝ ትራንስአክት ኢንተርናሽል ኃ/የተ/የግ/ማ/ |
በቅሎ ቤት |
ኦሮሚያ ክልል፣ሞጆ ከተማ፣የቦታ ስፋት 8338 ካ.ሜ ለኢንደስትሪ አገልግሎት የሚውል መጋዘን እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ባለአንድ ፎቅ ቤት ያለው፤ |
6000/2006 |
76,404,260.00
|
ሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡–
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(ibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል።
3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው::ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል::ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
4. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው::በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ ደግሞ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ይካሄዳል።
5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሊቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።
9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– አቡነ ጴጥሮስ ቅርንጫፍ 0111 26 61 31፣በቅሎ ቤት ቅርንጫፍ፡ 0114 65 52 26 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።