Reporter (May 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ OT/14/2025-26 (በድጋሚ የወጣ)
የደንብ ልብስ ግዥ ግልጽ ጨረታ
ኦሮሚያ ባንክ ለጥበቃ ሰራተኞች የሚሆን ጃኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ በሥራ ዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች ከታች በሰንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መልክ ለማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
|
ተቁ |
ዝርዝር |
መለኪያ |
ብዛት |
መግለጫ |
|
1 |
ጃኬት |
በቁጥር |
613 |
በተለያየ ልኬት ሆኖ በኔቪ ብሉ ከለር ( Different Size and Navy Blue color) |
1.ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 (ብር አንድ ሺህ) በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ ስር በሚገኘው የባንኩ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ በመክፈል ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ ከግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሣተፍ ይችላሉ::
አድራሻ
ግዥ አስተዳደር ዋና ክፍል
የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ዘጠነኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 9-002
ቦሌ መንገድ ከጌቱ ንግድ ማዕከል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0115572098/95
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከአንድ ናሙና ጋር እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
3. ጨረታው በተመሣሣይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
4. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኦሮሚያ ባንክ