Reporter (May 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር፡ ZB/22/26
ዘመን ባንክ አ.ማ የሰራተኞች ካፍቴሪያ እና ሬስቶራንት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሚሆን ድርጅት ጋር ለ1 (አንድ) ዓመት በሚቆይ የውል ስምምነት አገልግሎቱን እንዲያቀርብ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መካፈል የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መስያ /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አስባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒክ እና የዋጋ ሰነዶቻቸውን ዋና እና ኮፒ ስየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ብር ሁለት መቶ ሺህ ብቻ) በCPO ወይም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመክፈቻው ሰዓት በፊት ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታውን ሰነድ ታክስን ጨምሮ የማይመለስ ብር 230.00 (ብር ሁለት መቶ ሰላሳ ብቻ) በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6፡00 ሰዓት በባንኩ ግዥ እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. ጨረታው ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ሰንጋተራ፣ ራስ አበበ አረጋይ መንገድ፣የባንኩ ዋና መ/ቤት 15ተኛ ፎቅ ግዥ እና ሙል አስተዳደር መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘመን ባንክ አ.ማ
Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street,
P.O.Box 1212
Addis Ababa, Ethiopia
ፖ.ሳ.ቁ. 1212
ስ.ቁ +251 115 573 525 / +251 115 570 977
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ