የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች፣ ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ) ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች፣ ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ) ይፈልጋል


Reporter (May 10, 2026)

የንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን

  • ሕንፃዎች፣ ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና
  • ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ) ይፈልጋል።

1.1 ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ፡በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ኖኖ ወረዳ የቤት ቁጥር አዲስ ወይም በተለምዶ አጠራር ታጠቅ ደስታ መንደር ወደ ፌስቱላ ሆስፒታል ሕሙማን ማገገሚያ ማዕከል በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ይገኛል።

1.2 ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ መወዳደር ይችላል:: ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጹሁፍ፣ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) እና ሕጋዊ ውክልና መቅረብ አለባቸው።

1.3 ተጫራ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንና ሪፖርተር ጋዜጦች ላይ ከወጣበት ከግንቦት 2 ቀን 2018 . ጀምሮ ለአስር የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት ኦርጅናል ማህተም እና ፊርማ ያለበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01/05 የቤት ቁጥር 280 በተለምዶ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው በአካል መጥተው መግዛት ይችላሉ።

1.4 የጨረታው ሰነዱ (የጨረታ ቁጥር 04/2018) ብዙ ዝርዝር ገዳዮችን የያዘ መሠረታዊ ሰነድ በመሆኑ መግዛት እጅግ አስፈላጊ ነው።

1.5 ተጫራ ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ በመንተራስ 20%(ሀያ በመቶ) የማያንስ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ኤም.ኤፍ.አይ (CMED) ስም በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ መዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ግንቦት 17 ቀን 2018 . እስከ ረፋዱ 400 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። CPO (..) 20(ሀያ በመቶ) ካነሰ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።

 1.6  የጨረታው ሳጥን የሚቀመጠው በተ. 1.1 ተቀምጦ ባለው አድራሻ ንብረቶቹ በሚገኙበት ታጠቅ ደስታ መንደር የቤት ቁጥር አዲስ ኖኖ ወረዳ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ሸገር ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው።

1.7  የጨረታው ሳጥን ግንቦት 17 ቀን 2018 . ከረፋዱ 400 ሰዓት ተዘግቶ የእለቱ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 415 ሰዓት ይከፈታል።

1.8 አሸናፊው ወዲያውኑ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው .. (CPO) ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን 10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን መረከብ አለባቸው።

1.9 በተራ ቁጥር 1.7 መሰረት ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍለው የማይረከቡ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ቢድ ቦንድ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

1.10 የጨረታው አሸናፊ ከከም ዝውውር ጋር የተያያዘው ግብር እና ማንኛውም በመንግስት የሚጠየቁትን ክፍያዎች ይሸፍናሉ:: የስም ዝውውሩን ሂደት ተከታትለው ይፈፅማሉ ውዝፍ ዕዳ ካለ ግን አጫራች(ሻጭ) ይከፍላል።

1.11 የጨረታው ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ..(CPO)  የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

1.12  የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ማስታወቂያው በጋዜጦች ከወጣበት ግንቦት 2 ቀን 2018 . ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት (አስር ቀናት) እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 . እስከ 1000 ሰዓት ድረስ ብቻ የሚቆይ ይሆናል።

1.13  በተጨማሪም በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱት የተጫራቾች መመሪያን ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ከተጫራቾች ይጠበቃል።

1.14  የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌውሎሽፕ ኢንተርናሽናል (CMF) የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ...2920 አዲስ አበባ

.. 09 11 20 64 04 ወይም 09 44 35 45 19

የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሽፕ ኢንተርናሽናል (CMFI)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *