Reporter (May 10, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለአርዲ የግንባታ እቃዎች ማምረቻ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ የሚገኘዉንና በአቶ አንዱዓለም የሽዋስ ዓለሙ የካርታ ቁጥር AA000030901020 የቦታዉ ስፋት 150 ካሜ መኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል::
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት 40,248,433.62 (አርባ ሚሊዮን ሁለት አርባ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ62 ሳንቲም የሆነ
- ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል:
- በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል::
- የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል:: ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል::
- ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ::
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% (ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል::
- ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሰኔ 1/2018 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ:
ለተጨማሪ መረጃ፡– ፀደደ ባንክ ዋና መ/ቤት
በስ.ቁ +251918779825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል::