በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጉብሬ ዲስትሪክት 003/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባሥስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት /ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና ‹‹ኦሪጅናል›› እና አንድ ፎቶ ኮፒ በማለት አንድ የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ /ቤት የቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ::

4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።

5. አቀራቢዎች ጨረታ ሰነዱን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጎት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 600 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን 8:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

8. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የጉብሬ ዲስትሪከት /ቤት ፋይናንስና ሎጀስቲክስ

ስልክ ቁጥር፡– 0113 220 325 / 0113 220 327 / 0113 220 328

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *