Addis Zemen (May 12, 2026)
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 003/2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የወናጎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ከሀሴ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ባቀረቡት ጥያቀ መሰረት በ2018 በጀት ዓመት ዲች ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ሕጋዊ የግንባታ ሥራ ፍቃድ ያላቸዉ!
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ
- የዘመኑ ግብር የከፈለ /ከመንግሥት ዕዳ ነጻ የሆነ/፣
- ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባቢነት ካለዉ ተቋም መረጃ ማቅረብ የሚችል
- የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው ፤
- የ VAT ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- በግንባታ ሥራ ደረጃ BC/ GC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ TIN NO/
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
- አሸናፊ ድርጅት መክፍል ያለበትን የሽያጭ ታክስ 3% ይከፍላል።
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበርያ የአሸነፈበት ገንዘብ ልክ 10% ያስይዛል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የግንባታ ጨረታ ሰነድ የፋይናንስ ግዥ ን/አ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም ፋይናንሻል ኦርጅናል በአንድ ፖስታ ቴክንካል ኦርጅናል አንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒ እና ቴከንካል ኮፒ ለብቻ ታሽጎ በእናት ፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ “ማስከበርያ /CPO/ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) ማስያዝ ያለበት ሲሆን CPO ለብቻው ታሽጎ ኦርጂናል ቴክንካል ዶክመንት ጋር መቅረብ አለበት።
- ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የለባቸዉም።
- የሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን ሊገዙ ሲመጡ የግንባታ ሳይቱን አይተዉ ማረጋገጥ አለባቸዉ።
- ጨረታዉ የሚከፈተው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይተዉ በ22ኛዉ ቀን የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋው ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመሰብሰብያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- ማነኛዉም ተጫራች አንዱ ባቀረበዉ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
ማሳሰብያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጌዴኦ ዞን የወናጎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት