Addis Zemen (May 12, 2026)
የክትባት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ እና Syncronization Hommone
ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 408/18
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የክትባት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ እና Syncrorization Hormone ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
ሎት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ሰዓት |
ሰነድ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
የክትባት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ |
ሎት-1 |
በቁጥር |
5 |
200,000 |
በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል |
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
|
2 |
Syncronization Hormone |
ሎት2 |
Dose
|
15,000 |
200,000 |
በ16ኛው ቀን በ5፡00 ታሽጎ በዕለቱ 5፡30 ይከፈታል |
ደ/ኤ/ማ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ–ፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 16ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካና –ፋይናሻል የማጫረቻ ሰነዶች በአንድነት ፖስታ በማዘጋጀት በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣና የሚለይ ይሆናል።
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– 046-131–0134 ይጠቀሙ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ