በደቡብ ጎንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት የግንባታ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ጎንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት የግንባታ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (May 11, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት የግንባታ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግዥ መጠኑ ከብር 200 ሽህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1–3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ የመወዳደሪያ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።

6. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ከረዳት ገ/ያዦች ቢሮ ቁጥር 06 ፣09 እና 10 መግዛት ይቻላል።

7. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ታትሞ የሚቆይ ሲሆን፤ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 40 ይከፈታል።

8. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም።

9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው።

10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ እንዲሁም መስሪያ ቤቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን ሁሉም የእቃዎች ዋጋ መሞላት አለባቸው።

12. አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና ወይም ሳምፕል መሰረት ከሚፈለግበት ቦታ በራሱ ወጭ የሚያቀርብ መሆን አለበት።

13. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን፣ ፊርማቸውና ሙሉ አድራሻቸውን መግለጽና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።

14. በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል። እንዲሁም ሌሎች የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።

15. ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 25 02 44 መደወል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *