Addis Zemen (May 12, 2026)
ለ2ኛ/ሁለተኛ/ ጊዜ የወጣ የሀገር አቀፍ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ግዥ ጨረታ ቁጥር 002/2018
በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት የማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 ለወታደራዊ ስራ አገልግሎት የሚወሉ ወታደራዊ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁፐር (TIN NO) ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ
4. የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው አና ሌሎችንም ተጨማሪ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።
5. ተጫራቾቾ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000(ሶስት መቶ ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢንድ–ቦንድ የባንክ ዋስትና ለደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል፣
6. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ የኮሚሽኑ B አካዉንት ቁጥር 1000514294098 ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ በማቅረብ በሚዛን አማን ከተማ በርጌስ በሚገኘዉ በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ከ/መ/የማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የግዥና ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለብቻ በኢንቨሎፕ በማሸግ በትልቅ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ።
8. ተጫራቾች አያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመጻፍ እና በመፈረም ኦሪጅናል አና ኮፒ የሚል ጹሁፍ በግልጽ ማስፈር አለባቸዉ።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ– ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ዕለት በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀዉ ዝርዝር መሠረት ናሙናዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለባቸዉ ሲሆን ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የለውም።
የተገዙ ዕቃዎች የጭነት ማጓጓዣ ወጪ በአቅራቢ /በአሸናፊ/ድርጅት የሚሸፈን ሆኖ ርክክብ የሚፈፀመዉ ከአ/አበባ ሚዛን አማን 600 ኪ/ሜ በአማን የሚዛን ማረሚያ ተቋም መጋዘን ይሆናል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት የማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ በሚዛን ከተማ በርጌስ ከመስቀለኛ መንገድ ወደ አርጌ ማረሚያ ተቋም በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢሮ 2ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 047 135 8991 መጠየቅ ይቻላል።
የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን