Addis Zemen (May 12, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ አመታዊ መጽሔት ማሳተም ይፈልጋል፡፡
የመፅሄቱን አይነት በሚመስከት እንደሚከተለው ሆኖ፡–
- የውጭ ሽፋን / ከቨር ፔጅ /250 ግራም
- የውስጥ ገጹ 180 ግራም
- ከለር ፕሪንት/ ባለቀለም የሆነ ወረቀት
- የገጽ ብዛት 45 የሆነ መጽሔት መስፈርቱን ከሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡
መመዘኛዎች፣
- በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት
- የዘመኑን ግብር የከፈለች
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ላት
- የVAT 15% ተመዝጋቢ የሆነች፤
- የንግድ ምዝገባ አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ማስረጃ ያለው/ላት፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የብር 5,000/አምስት ሺህ ብር/CPO/ተመሳሳይ/ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች፡– ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት /ፕሮፎርማ/ ነጠላ ዋጋ ከነማስረጃው ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አዘጋጅተው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ህጋዊ/ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኮሚሽኑ ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት /ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡በተጨማሪም የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት እያስተጓጉልም::
- ኮሚሽኑ (መ/ቤቱ) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፤ –ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተደዳደር ኮሚሽን ሀላባ ቁሊቶ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465562209 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን