የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ፎቶና ቪዲዮ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው፣ ኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ሀርድ ዲስክ፣ የላፕቶፕ ቦርሳ፣ UTP- Cable 305 m፣ RJ 45 With Jacket እና D-Link 8 Port በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ፎቶና ቪዲዮ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው፣ ኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ሀርድ ዲስክ፣ የላፕቶፕ ቦርሳ፣ UTP- Cable 305 m፣ RJ 45 With Jacket እና D-Link 8 Port በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር 001

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን 2018 በጀት አመት ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚውሉ

  • በሎት 1 ፎቶና ቪዲዮ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው ፣ኮፒ ማሽን ፣ፕሪንተር ሀርድ ዲስክ፣ የላፕቶፕ ቦርሳ UTP- Cable 305 m RJ 45 With Jacket እና D-Link 8 Port በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

መመዘኛዎች፣

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመደቡ
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
  3. VAT 15% ተመዝጋቢ የሆኑ
  4. የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት ከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ CPO፣ቼክ፣ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማቅረብ የሚችሉ
  5. አሸናፊው ተጫራች ማንኛውንም ወጪ በራሱ ሸፍኖ በኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችል
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች፡ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በሎት 1ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ነጠላ ዋጋ ከነማስረጃው ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8.  ጨረታው 10ኛው ቀን ከቀኑ 1130 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ/ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው ቀን ከረፋዱ 430 ሰዓት በኮሚሽኑ ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡በተጨማሪም የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
  9.  ኮሚሽኑ (/ቤቱ) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ሀላባ ቁሊቶ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465562209 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች

አስተዳደር ኮሚሽን