Be'kur (May 11, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ሙሉጌታ አምሳል እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ደሳለው ሽቴ መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአገው ግምጃ ቤት ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ግርማው አለማየሁ፣ በምዕራብ ተስፋየ ብዙነህ፣ በሰሜን የቀበሌ ቤት እንዲሁም በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው በአቶ ደሳለው ሽቴ ስም የተመዝግቦ የሚገኘው ቤት በመነሻ ዋጋ በብር 732,360.50 (ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ስለሚሸጥ ከግንቦት 05/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 05/2018 ዓ.ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ሰኔ 05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት