የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ ለፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ ግዥ እና የሙዚቃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ ለፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ ግዥ እና የሙዚቃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ////መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ //ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ

  • ሎት 1የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 2ለፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ ግዥ
  • ሎት 3የሙዚቃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 በመሆኑም በጨረታ

  1. ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ለሎት 1 የሻይ ቡና መስተንግዶ ግዥ 50,000 ብር ሎት 2የፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ 50,000 ብር ሎት 3የሙዚቃ መሳሪያ 50,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6.  ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  8. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 830 ታሽጎ በዚያው ቀን 900 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  9. ይህ ጨረታ 60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል
  10.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *