Be'kur (May 11, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግንባታው ተቋርጦ የነበረውን የጭልጋ ማረሚያ ቤት የምድረ ግቢ፣ የመንገድ፣ የውሃ እና የኤሌክትሪክ ስራዎች እንዲሁም ቀሪ የህንፃ የማጠናቀቂያ ስራዎች ግንባታ አስገንብቶ ለማጠናቀቅ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ የዘርፉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላ ላችሁ፡-
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናልና ኮፒ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታስክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚሞሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 500‚000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው።
4. የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሥራ ደረጃቸው GC-2 እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ፣ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር-11 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የስራ ፈቃዳቸውን በማሳየት ብር 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር-11 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ለቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታ።
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የሥራ ዝርዝር መግለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳንዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች በሞሉት ነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው።
10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ፣ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸውን በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 14 ማቅረብ ይችላሉ።
13. .መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
14. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር-11 ድረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058-226-6035 ባህር ዳር በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን