የአብክመ ውሀና ኢነርጅ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዮ ፕሮግራም በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ እና የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአብክመ ውሀና ኢነርጅ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዮ ፕሮግራም በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ እና የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (May 11, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-0011/2018

የአብክመ ውሀና ኢነርጅ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዮ ፕሮግራም በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ እና
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1. የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፣ ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  6. በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100. (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት።
  9. የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 0132 /058 220 10 87 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ።
  12. አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቀበሌ 07 ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት ነው።

የአብክመ ውሀና ኢነርጅ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *