Addis Zemen (May 12, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር– አ/አ/ባ/ኪ/ቱ/ቢ/003/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ለ2018 በጀተ ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአፈፃፀም ብቃት ላይ ተመስርቶ በሚቆይ የአንድ ዓመት የኮንትራት ውል እና የተወሰኑትን ዕቃዎች አገልግሎቶች ለአንድ ጊዜ ብቻ መግዛት ይፈልጋል፡
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወቀረት፣ ተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN NUMBER/ እና 6 ወር ያልበለጠው ወቅታዊ በጨረታ ለመሳተፍ እንድችሉ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የጨረታ ተሳትፎ ፈቃድ/TAX CLEARANCE/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን በሚወዳደሩበት እያንዳንዱ ሎት ፊት ለፊት የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በዋናው የቴክኒክ ሰነዳቸው አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም. የተፃፈ እና በጽ/ቤት ኃላፊ የተረጋገጠ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. የኮንትራት ውል የሚፈፀሙ
|
በዓመታዊ የውል አገልግሎት የሚፈፀም |
||
|
ሎት1 |
የፅዳት አገልግሎት |
25000.00 |
|
ሎት2 |
የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት |
25000.00 |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ አራዳ ጊዮርጊስ ከቀይ መስቀል ጀርባ አዲስ ካፒታል ባሰራው ህንፃ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ–ጥበብ ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 7ኛ ፎቅ፣ በመክፈል ከ7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ (7ኛ ፎቅ፣ ) ሰነዱን በሶፍት ኮፒ፤ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት እስከ 11ኛው /አስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሰነዱን ዋና በኢንቬሎፕ እንዲሁም ቅጂ በኢንቬሎፕ በማሸግ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ (7ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 701) ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው /አስራ አንደኛው/ ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 701 ይከፈታል። 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተያዘለት ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
4. ተጫራቾች እንደ ጨረታው ባህሪ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው አገልግሎቶችና ዕቃዎች ተገቢውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እያንዳንዱን ዕቃ /አገልግሎት የመጫረቻ ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር መግለጫ/Specification/ እና መለኪያ መሠረት ቫትን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እንደ ጨረታው ባህሪ/ቴክኒካል መስፈርተር ላለው ለእያንዳንዱ ሎት እንዳስፈላጊነቱ የቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሠነድ ዋና እና ቅጂ በማዘጋጀት በእያንዳንዱ ኢንቬሎፕ የሎቱን ዋና እና ቅጂ በግልጽ በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች በተ.ቀ.1. የተዘረዘሩትንና ሌሎች በጨረታ ሠነዱ ውስጥ የተገለጹ አስፈላጊ መረጃዎችን ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011-126 4586 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ–ጥበብ ቢሮ