የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ለማሠራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/08/2018

1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ለማሠራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEP Transmission Substation Construction አካውንት ቁጥር 1000252665203 ገቢ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ትሬዠሪ አስተዳደር ቢሮ ደረሰኙን በማስመራት የጨረታ ሰነዱን ሕዳሴ ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/ GBP/NCB/08/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሕዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል።

7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-557 4011 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *