Addis Zemen (May 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/09/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/09/2018 ብሎ በመጻፍ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት1. ፈርኒቸር |
ሎት 1. ብር 100,000.00 |
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
ሎት-2. ኤሌክትሪክ እቃዎች |
ሎት 2. ብር 100,000.00 |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116732190 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል