የኮምቦልቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው የ2018 በጀት ዓመት የፅዳት እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኮምቦልቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው የ2018 በጀት ዓመት የፅዳት እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 11, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኮ/ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው 2018 በጀት ዓመት የፅዳት እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፍቃድ ያሳደሱ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው::

2. የግዢ መጠን 200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራቁ 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን አና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ቀን ባይገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከፍቶ ከማወዳደር የማያግደው መሆኑ ይታወቃል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬው የጠቅላላ ዋጋውን 2% ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በኮ/ 03 ጤና አጠ/ጣቢያ ገዥ/ፋይ//አስ/ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይቻላል።

6. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በማስታወቂያ ቦርድ ላይ ይቆያል።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ የታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ/ 03 ጤና አጠጣቢያ በግዥ/ፋይ/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 ይከፈታል።

9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም አይኖርም ያልተሞላ አይተም ካለ ከውድድር ወጭ ይሆናል።

10. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው።

12. ተጫራቶች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የተጠየቁትን መረጃ አሟልተው ካልተገኙ በጨረታው ላይ አይሳተፉም፡፡

13. አሸናፊው በራሱ ወጭ አቃዎችን ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይሮርበታል።

14. ጨረታው 40 ቀናት ተወስኖ ይቆያል።

15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 351 07 39 / 0967 679 393 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *