ፀደይ ባንክ ቆጋ ቅርንጫፍ የቦታዉ ስፋት 1473.077 ካሬ ሜትር የቦታዉ አገልግሎት ለኢንዱስትሪ የሆነ ቤት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ማጫረት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ ቆጋ ቅርንጫፍ የቦታዉ ስፋት 1473.077 ካሬ ሜትር የቦታዉ አገልግሎት ለኢንዱስትሪ የሆነ ቤት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ማጫረት ይፈልጋል


Be'kur (May 11, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

አቶ አዱኛ ሙጨ በፀደይ ባንክ ቆጋ ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በመያዧ የተያዘዉን በአቶ አዱኛ ሙጨ ስም የተመዘገበ በመርዓዊ ከተማ 03 ቀበሌ በካርታ ቁጥር 1344/2014 በአዋሳኝ በሰሜን፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ መንገድ እንዲሁም በደቡብ አስራት አቤ የሚዋሰንና የቦታዉ ስፋት 1473.077 ካሬ ሜትር የቦታዉ አገልግሎት ለኢንዱስትሪ የሆነ ቤት ሰኔ 6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ባለዉ ጊዜ በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 3,335,811.4 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ሽህ ስምንት መቶ አስራ አንድ ብር ከአራት ሳንቲም) ይሸጣል። በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለሚያሟሉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ማጫረት ይፈልጋል።

ደንቦች እና ቅድመ ሁኔታዎች፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን ¼ ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለመጫረት ሲቀርቡ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅርብ አለባቸዉ።
  3. ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ ሰዉ ዉክልና እና የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ድርጅቱ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት።
  4. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ ከቦታዉና ቤቱ ጋር የተያያዘ ክፍያ እንዲሁም ስም ለማዞር የሚወጡ ወጭዎች በተጫራች በገዥ የሚሸፈን ይሆናል።
  5. የጨረታ አሸናፊዉ የጨረታ ዉጤቱ በሚመለከተዉ አካል ፀድቆ አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል።
  6. የጨረታ አሸናፊዉ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉዉን ገንዘብ ገቢ ካላደረገ ያስያዘዉን 1/4 ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ እንደገና ይወጣል።
  7. ጨረታዉ የሚካሄድበት ቦታ መርዓዊ ከተማ ከሚገኘዉ ፀደይ ባንክ ቆጋ ቅርንጫፍ ይሆናል።
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ይችላሉ።
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 1154 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

ፀደይ ባንክ ቆጋ ቅርንጫፍ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *