Addis Zemen (May 13, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥሬ ስንዴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፌታድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
5. ስለ ጥሬ ስንዴው አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 106/107 ማግኘት ይችላሉ፣
8. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ / ለጥሬ ስንዴ ጎንደር ብቻ ለመወዳደር ብር 300,000.00 / ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ፡ ደብረ ብርሀን ብቻ ለመወዳደር ብር 300,000.00 / ሶስት መቶ ሺህ ብር/፡ ሁለቱም ሃገር ለመወዳደር ብር 400,000.00/አራት መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና / Unconditional Bank Garntee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፣
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት።
11. ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ስ/ስ/አ/ኮሚሽን ትልቁ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፣
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
የገዥ መ/ቤት አድራሻ ኢብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን ባህር ዳር
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 058 218 0014 / 058 218 1103
በአብክመ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና
ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን