Addis Zemen (May 14, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለድሬድዋ ሁ/ስ/መሪ/ማ/ቤት አገልግሎት የሚውል የጀኔረተር ስለተበላሽ ጥገና ለማሰጠገን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰጠገን ይፈልጋል
|
ተ/ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
|
1 |
ለድሬድዋ ሁ/አ/መረ/ማ/ቤት የጀኔረተር ጥገና ገዥ |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለጸ መሆን አለበት።
2.የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የታደሰ የዘመኑንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያመጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምርክ ባለ ስልጣን የዘመኑ ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
5. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቀረብ አይቻልም።
6. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናለፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት 100,000.00 ብር ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው
7. እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያም በላይ መሆን ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቀረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
9. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በስም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እናበሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ፒያሳ አ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሲስ ኮሚሽን ከፍ ብሎ በሚገኘው ፌዴራሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ዋናው መ/ቤት 1ኛ ፎቅ የገዥና ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ስነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
12. ጨረታው 09/09/2018ዓ.ም ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በመ/ቤቱ መስብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል
13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፣
14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
15 ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0111-26-56-65 / 0111 265 99 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን