የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለቢሮ እና ተዛማጅ ለሆኑ አገልግሎቶች ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለቢሮ እና ተዛማጅ ለሆኑ አገልግሎቶች ማከራየት ይፈልጋል


Reporter (May 24, 2026)

የህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለቢሮ እና ተዛማጅ ለሆኑ አገልግሎቶች ማከራየት ይፈልጋል

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍን የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን የሚፈልጉ ጀምሮ ባሎት 10 (አስር ) ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ::

1. አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

2. የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እንዲሁም ከሠዓት ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋ/መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፤

3. ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ህንፃው የሚገኝበት ቦታ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ

4 ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 4:30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ WAT/ ማሳየት አለባቸው!

7. ጨረታው ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡3ዐ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤

8. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤

10.የጨረታው አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በተገለፀ በ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ ሌላ አማራጭየሚወስድ ይሆናል፤

11.ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

12 ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል::

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

አድራሻ፦ በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *