የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው ህንጻ ውስጥ ያለውን ቢሮ የውስጥ ELV (Extra low Voltage System) እና የካሜራ ዝርጋታ የዲዛይንና ግንባታ (Design Build) ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት አ/ማህበር ባስገነባው ህንጻ ውስጥ ያለውን ቢሮ የውስጥ ELV (Extra low Voltage System) እና የካሜራ ዝርጋታ የዲዛይንና ግንባታ (Design Build) ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 24, 2026)

የቢሮ ውስጥ የኔትወርክ እና ካሜራ ዝርጋታ ጨረታ

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት /ማህበር ባስገነባው ህንጻ ውስጥ ያለውን ቢሮ የውስጥ ELV (Extra low Voltage System) እና የካሜራ ዝርጋታ የዲዛይንና ግንባታ (Design Build) ሥራውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾችን ELV System Integration ወይም IT ላይ ተሰማርተው 2018. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያላቸው

2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN)

3. 2017 . ከግብር ዕዳ ነፃ የሆኑበትን ሰርተፊኬት፤

4. ለሚቀበሉት ክፍያዎች ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፤

5. በዘርፉ ተሰማርተው ለሰሩት ስራ በቂ የስራ ልምድ ማቅረብ እና የሰሩትን ስራም ማሳየት የሚችሉ

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በመያዝ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከማህበሩ /ቤት በመውሰድ ዋጋቸውን ሞልተው ለጨረታ ማስከበርያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከታች በተገለፀው ሰዓት የሰነዶቻቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 900 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ /ቤት ይከፈታል

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ቅናሽ ዋጋ የመምረጥ ግዴታም የለበትም።

ማስታወሻ

  • አድራሻ ኮልፌ አጣና ተራ ከቴሌው ጀርባ የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት /ማህበር ብሎክ 2 አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
  • የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የሚቻለው ከጠዋት 230 እስከ 630 ከሰዓት 730 እስከ 1030 ብቻ ይሆናል፤

ስልክ ቁጥር 09-32-08-03-77 ወይም 09-12-05-47-92

የኮልፌ ቅዱስ ራጉዔል አዲስ ሕይወት /ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *