የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አክሲዮን መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አክሲዮን መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በፍርድ ባለዕዳ እነ ሐወኒ አሸናፊ 2 ሰዎች መካከል ያለውን ክርክር አስመልክቶ፡አዋሽ 1 እና 2 ደረጃ ትምህርት ቤት /የተ/የግ/ማህበር አክሲዮ 3,808(ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት) የሆነ እና የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1,000 አንድ ሺህ ከሆነ ውስጥ የፍርድ ባለዕዳ ጠቅላላ የአክሲዮን ድርሻ 3,758(ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት) ጠቅላላ የአክሲዮኖቹ ዋጋ 3,758,000(ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ) በሆነ መግዛት የሚፈልግ አካል በሲፒኦ የመነሻውን ግምት ብር 25% በማስያዝ ማህበሩ በሚገኝበት ቦታ ቀርበው ግልጽ በሆነ ጨረታ በቀን 15/10/2018 ሰዓት 300 እስከ 630 ማህበሩ በሚገኝበት ቦታ የጨረታ ኮሚቴ መግዛት የሚፈልጉትን ሰዎች አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን፣ መግዛት የሚፈልግ ቀርቦ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  1. የጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ 30 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በኦሮሚያ ከለቻ ጋዜጣ፣ በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግቢ ማስታወቂያ በሚለጠፍበት ቦታ እና በአዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ተለጥፎ የሚቆይ ይሆናል።
  2. መግዛት የሚፈልግ ሰው/ድርጅት/ ግምት ዋጋ ብር 3,758,000(ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ) የጨረታ መነሻ በሲፒኦ 25% አስይዞ መቅረብ አለበት።

የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *