Addis Zemen (May 31, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ECMA/NCB/17/2018
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለው በጀት የኢ.ኤም.ኤ መዋቅር ጥናት የምክር አገልግሎት (The Organizational Re-structuring Study of ECMA consultancy services) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ከፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገን የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ሰኔ 08 ቀን 2018 ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ9:30 ላይ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/ መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ፣ ክ/ከተማ ቂርቆስ፣ ወረዳ 9 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ 011-5-57-83-27
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን