Addis Zemen (Jun 06, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የድርጅቱ ስም የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በባለቤትነት የሚያስተዳድራቸውንና ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ሱቆችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ
- የሱቆች ብዛት፡– 4
- የሱቆች አድራሻ፡– አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሲ.ኤም.ሲ መንገድ
- የሱቆች ስፋት፡ 32 ካሬ ሜትር (እያንዳንዳቸው)
- የአገልግሎት አይነት ለንግድ
2.ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 202 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. አጠቃላይ መመሪያዎች
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-646-3315 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾቹ የሚከራዩትን ሱቅ አስቀድመው መጎብኘት የሚችሉሲሆን፣ የቀረበው የኪራይ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ