የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ ለሚገናባው ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የTempered Glass Work አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ ለሚገናባው ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የTempered Glass Work አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 50/2018

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ ለሚገናባው ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የTempered Glass Work አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመክፈላቸው የሚሰጥ ማስረጃ ያለው/ያላት፤ አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ከዚህ በፊት ለመስራታቸው ህጋዊ ከሆነ ተቋም የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

2. የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣

3. የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውስድ ይችላሉ፤

4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳር ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን/ግብ/ግዥ እና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮ ክፍል ነው።

5. ውድድሩ በሎት /በጥቅል ዋጋ የሚታይ ይሆናል፤ ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ባ/ዳር 058-218-05-38/09-18-01-06- 17/09-13-27-60-57
አዲስ አበባ ፡- 011-126-56-52/5145/0912085639

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *