በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት የጤና ጣቢያ አጥር ግንባታ በጨኪ ቀበሌ ለማሰራት ደረጃቸው በጂሲ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም በቢሲ ህንጻ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 8 እና በላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት የጤና ጣቢያ አጥር ግንባታ በጨኪ ቀበሌ ለማሰራት ደረጃቸው በጂሲ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም በቢሲ ህንጻ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 8 እና በላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 28, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018

ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት የጤና ጣቢያ አጥር ግንባታ በጨኪ ቀበሌ ለማሰራት ደረጃቸው በጂሲ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም በቢሲ ህንጻ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 8 እና በላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TN No ያላቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ግንባታውን በውለታው ጊዜ ውስጥ በአይነት፣ በመጠን እና በጥራት ሳያጓድል መገንባት የሚችል::

3. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግም ሆነ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን እና አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ወይም የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት በመሂ 1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የእቃ ግዥ መ/ቤቱን፣ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ በማ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በዚሁ እለት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡

6. 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል።፡

7. የመልካም የሥራ አፈጻጸም ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

8. ሥራውን በተሰጠው ማስረጃ ዲዛይን መሰረት ውስጥ ሰርተው ማጠናቀቅ የሚችሉ፡፡

9. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000/ሃያ ሺህ/እና ለአገልግሎት ከብር 10,000/ አስር ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ግንባታ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የሥራ ዝርዝር መሰረት በውሉ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡

12. የጨረታ ሰነዱን በጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግስት የሥራ ሰዓት ለእያንዳነዱ ሰነድ በማይመለስ 500 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡

13. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

14. ማ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ማ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደሴ መስመር ላይ ነው፡፡

16. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 89 00 301/011 632 0604 ደውለው ይጠይቁ፡፡

በአ/ብ/ክ/መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *